Discover our stories through the power of sound. Listen Ethiopia is a dedicated space where the beauty of Ethiopian literature comes to life through sound. We explore the art of writing by offering clear guides and examples on various essay styles, while also celebrating the legacies of iconic Ethiopian authors through their biographies and photos. To honor our literary heritage, we have transformed a selection of the finest contemporary short stories into engaging audio narrations, bringing the heart of our culture and history directly to your ears
Our mission is centered on accessibility and inclusion. While these narrations are for everyone, they are specially designed to provide a rich source of entertainment and knowledge for the blind and visually impaired. Additionally, to support Amharic language learners, we provide bilingual content that makes it easier to follow along. Whether you are here to learn or to be inspired, we invite you to discover Ethiopia’s stories through the power of the spoken word.
በ"ኢትዮጵያ እናድምጥ" የድረ-ገጻችን ክፍል በብዛት ስለ ድርሰት (Essay) እና ደራሲያን (Authors) የሚያብራራ ሲሆን፤ በውስጡም የድርሰትን ምንነት፣ ዓይነቶችና ማሳያ ምሳሌዎችን (Examples) በጽሑፍ ያካተተ ነው። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ደራሲያንን ምስል (Photo) እና የሕይወት ታሪክ (Biography) በጥቂቱ የምንዳስስበት ሲሆን፤ የዘመናችንን ታዋቂ ደራሲያን ሥራዎች ለእናንተ ለማድረስ ከአንድ ስመ-ጥሩ ደራሲ መጽሐፍ (Book) ውስጥ የተመረጡ ምርጥ አጫጭር ልቦለዶችን (Short Stories) በትረካ በተዘጋጀ መልኩ አቅርበናል።
ይህ ትረካ ለሁሉም ተጠቃሚዎቻችን የሚያገለግል ቢሆንም፤ በተለይ ማየት ለተሳናቸው (Blind persons) እና የእይታ ችግር (Visual impairment) ላለባቸው ወገኖቻችን የመዝናኛና የቁም-ነገር ምንጭ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ዓላማውም የሀገራችንን ሥነ-ጽሑፍ፣ ባህል (Culture) እና ታሪክ (History) በተረኩት የልቦለድ ታሪኮች ውስጥ በቀላሉ እንዲረዱ ለማድረግ ነው። በተጨማሪም አዲስ አማርኛ ቋንቋ ለሚማሩ (Amharic Language Learners) ተማሪዎች እንዲያገለግል በማሰብ፣ የገጹን የተወሰኑ ክፍሎች በሁለት ቋንቋዎች (Bilingual) ለማቅረብ ሞክረናል።
I am a Grade 11 student currently exploring the intersection of technology and storytelling. This project was born when my teacher challenged us to design a website; I immediately knew I wanted to build something that honored our rich heritage of "Dirset" (ድርሰት). I believe that our creative writing history is a living guide for our present. By documenting these works and the lives of those who wrote them, I hope to ensure that the wisdom of "yesterday" continues to inspire us today.
Beyond preservation, I wanted this platform to be a space of true inclusion. I realized that the beauty of our literature is often inaccessible to the blind community, so I integrated audio narrations to bridge that gap. To me, a professional website should be more than just code; it should be humanized to serve everyone. My goal is to create an experience where the power of the written word can be heard and felt by all, making the art of Dirset accessible to every heart and ear.
እኔ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ስሆን፤ ይህ ድህረ-ገጽ የታሰበው የመምህራችንን የዌብ ሳይት ስራ ፈጠራ ጥሪ ተከትሎ ነው። ጥበብና ቴክኖሎጂን በማጣመር፣ ለሀገራችን ድንቅ የድርሰት ታሪክ እውቅና የሚሰጥ መድረክ ለመፍጠር ወሰንኩ። ድርሰቶቻችን ማንነታችንና የታሪካችን አሻራ በመሆናቸው፣ ትላንት በብዕር የተከተቡት ድንቅ ስራዎች ለዛሬው ትውልድ ብርሃንና መመሪያ እንዲሆኑ ማስቻል ዋነኛ ፍላጎቴ ነው።
ይሁን እንጂ ድረ-ገጹ ፕሮፌሽናል ብቻ ሳይሆን የሰብአዊነት ስሜትም እንዲኖረው ፈልጌያለሁ። የአይን ስውራን ወገኖቻችን ከድርሰት አለም ጋር ያላቸው ግንኙነት የተገደበ መሆኑን በመገንዘቤ፣ በድረ-ገጹ ላይ የድምፅ ትረካዎችን አካትቻለሁ። ጥበብ ለሁሉም እኩል ተደራሽ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ። ዓላማዬ ማንኛውም ሰው ያለምንም እንቅፋት የድርሰቶቻችንን ጣዕም እንዲያጣጥም በማድረግ፣ ቴክኖሎጂን ለሰው ልጆች ሁሉ ድልድይ እንዲሆን መጠቀም ነው።