Listen Ethiopia


ድርሰት

ድርሰት ማለት አንድ ጸሐፊ ሀሳቡን፣ ስሜቱን፣ እውቀቱን ወይም ምናቡን በጽሁፍ በማደራጀት ለንባብ የሚያቀርብበት የስነ-ጽሁፍ ጥበብ ነው፣። የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ፣ መረጃ ለመስጠት ወይም ታሪክ ለመንገር የሚያገለግል፣ የተዋቀረ የቃላት አጠቃቀም ጥበብ ነው። በአጠቃላይ ድርሰት የሰውን አእምሮ የሚቀርጽ፣ ታሪክንና ስልጣኔን የሚያስተላልፍ ጥበባዊ የጽሁፍ ስራ ነው ።

የሰው ልጅ የራሱን እምነት ፣ ገጠመኝ፣ ተስፋ እና አመለካከት፣ በአጠቃላይም ማሀበራዊህይወት በሌላ ቦታ ርቆ፣ ለሚኖር መሰል ፈጡር መልእክት ወይም ታሪክ ለማስተላለፍ ወይም ለማድረስ ሢል በቸግሩ ምክንያት የፈጠረው የንግግር ወኪል ጽሑፉ ነው። ድርሰት ታሪክን/ባህልን/ ከዘመን ወደ ዘመን፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከስፍሯ ወደ ስፍራ ለማስተላለፍ ያስቻለ የሰው ልጅ የፈጠራ ውጤት።

ዋና ዋና የድርሰት ነጥቦች፦
አላማ፦ መናገር፣ ማስተማር፣ ማዝናናት ወይም ማሳመን።
አይነቶች፦ ተራኪ፣ ገላጭ፣ አሳማኝ እና አብራሪ ድርሰቶች።
ክፍሎች፦ መግቢያ፣ አካል እና ማጠቃለያ።

ማንኛውም ድርሰት መግቢያ፣ ማዕከላዊ ክፍል እና መደምደሚያ የተሰኙ ሦስት መሠረታዊ ክፍሎች አሉት። መግቢያው አንባቢን በመሳብና ፍንጭ በመስጠት ወደ ሐሳቡ የሚያስገባ ሲሆን፣ ማዕከላዊ ክፍሉ ደግሞ ዋናው መልዕክት በሰፊው የሚብራራበት የድርሰቱ አካል ነው። መደምደሚያው ደግሞ የተነሱትን ሐሳቦች በአጭሩ ሰብስቦ በማቅረብ ድርሰቱን በስኬት ይቋጫል።

የድርሰት ዓይነቶች

ተራኪ ድርሰት

ተራኪ ድርሰት መልዕክትን በታሪክ ወይም በተረት መልክ የሚያቀርብ የድርሰት ዓይነት ሲሆን፣ አቀራረቡም ሙሉ በሙሉ ትረካዊ ነው። በዚህ የድርሰት ዘይቤ ውስጥ ማንኛውም ድርጊት ወይም ክስተት የተፈጸመበት ሁኔታ በጊዜ፣ በድርጊት እና በተጠይቅ (ምክንያትና ውጤት) ቅደም ተከተል ተዋቅሮ ይቀርባል። ትረካውም "እንዲህ ነበረ፣ እንዲህ ተደረገ፣ እንዲህ ሆነ..." በሚሉ አገላለጾች የታጀበ ሆኖ፣ አብዛኛውን ጊዜ በኃላፊ ጊዜ ላይ በመመስረት በኃላፊ ጊዜ አመልካች ግሶች አማካኝነት ይተረካል። እንደ ግለሰብ የሕይወት ታሪክ፣ የጦርነት አነሳስና ፍጻሜ፣ እንዲሁም የአንድ ከተማ አመሰራረት ያሉ ታሪካዊና ማኅበራዊ ኩነቶች በዚህ የድርሰት ዓይነት የሚቀርቡ ዋነኛ ምሳሌዎች ናቸው።

ሥዕላዊ ድርሰት

ሥዕላዊ ድርሰት (Descriptive): ይህ አይነት ድርሰት የአንድን ነገር፣ ቦታ ወይም ሰው መልክና ባህሪ ቁልጭ አድርጎ በመግለጽ አንባቢው በአእምሮው ሥዕል እንዲስል የሚያደርግ ነው። ለምሳሌ የአንድን ተራራ ግርማ ሞገስ ወይም የአንዲትን ጀግና ሴት ገጽታ የሚገልጽ ጽሑፍ ሥዕላዊ ድርሰት ይባላል።

ገላጭ ድርሰት

ገላጭ ድርሰት (Expository): መረጃን፣ እውነታን ወይም ጽንሰ-ሐሳብን ለሌላ ሰው ለማብራራት እና ግንዛቤ ለመስጠት የሚጻፍ ነው። ለምሳሌ "ቡና እንዴት ይዘጋጃል?" ወይም "የኢንተርኔት ጥቅም ምንድነው?" የሚሉ ጽሑፎች መረጃን ስለሚገልጹ በዚህ ሥር ይመደባሉ።

አከራካሪ ወይም አሳማኝ ድርሰት

ጸሐፊው የራሱን አቋም በመያዝ፣ አንባቢው ያንን ሐሳብ አምኖ እንዲቀበል ለማሳመን ማስረጃዎችንና አመክንዮዎችን የሚያቀርብበት የድርሰት ዓይነት ነው።

ድርሰት

"የብዕር ትርታና የቃላት እስትንፋስ"

"The Pen’s Pulse and the Breath of Words."